እንኳን ደስ አላችሁ

የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስቴር የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በየዓመቱ በሚያስመዘግቡት ውጤት እየመዘነ ለዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ ይሰጣል፡፡ በ2009 ዓ.ም. ዩኒቨርሲቲዎቹ የነበራቸውን አፈፃፀም መሰረት አድርጎ ዛሬ ይፋ ባደረገው ደረጃ የመጀመሪያው ትውልድ (አንጋፋ) ውስጥ ከሚመደቡት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ዩኒቨርሲቲያችን የ3ኛ ደረጃን አግኝቷል፡፡
ለተገኘው ውጤት የመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ አባላት አስተዋፅዖ ከፍተኛ በመሆኑ ጥረታችን ውጤት በማፍራቱ እንኳን ደስ አለን እያልን በ2010 ዓ.ም. አንድነታችንን አጠናክረን በመስራት ከዚህ የተሻለ ውጤት እንደምናስመዘግብ እርግጠኞች ነን፡፡
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ

Our University is ranked 3rd from first generation Universities in Ethiopia based on  2009 E.C. performance evaluation made by the Ministry of Education. In recognition, our University has received an award and recognition of excellence certificate from the ministry. Congratulation for all, as this result is obtained because the University academic and administration staff, students, and the University leadership at different level owned the University tasks; worked hard in cooperation with the surrounding community and in a team spirit. We have to perform best in continuity and change our commitment in to best excellence to achieve the vision of our University. Yes, we can excel together!

Haramaya University

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *